የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ወር በVirginia

የVirginia የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ የራስጌ ምስል 2022

ፌብሯሪ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ወር ነው። በVirginia ውስጥ ስላለው የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ እና ማክበር ስለሚቻልበት መንገዶች ተጨማሪ ይወቁ።

ልዩ ትኩረት

በመላው የፌብሯሪ ወር በVirginia ታሪክ ውስጥ ስመ ጥር የሆኑ ጥቁር ወንዶች እና ሴቶች ተለይተው ይቀርባሉ።

Maggie L. Walker

ተለይተው የቀረቡ ሴት

Maggie Lena Walker ጥቁር አሜሪካዊ ነጋዴ እና መምህር ነበሩ። Walker በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ባንክ ማቋቋም የቻሉ እና ባቋቋሙት ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊ ሴት ነበሩ። Walker በመሪነት ሚናቸው በኩል በጥቁር አሜሪካውያን የአኗኗር ዘይቤ ላይ ተጨባጭ ለውጥ የማምጣት ራዕይ አንግበው ስኬታማ መሆን ችለዋል።

ስለ Maggie L. Walker ተጨማሪ ለማወቅ

የStan Maclin ፎቶ

Stan Maclin

ተለይተው የቀረቡ ወንድ

ስታን ማክሊን (ታህሣሥ 27 ፣ 1953-ጃንዋሪ 11 ፣ 2021) በማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር የማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት ያለመታዘዝ መልእክት አነሳሽነት ተፈጥሯል። የሜኖናዊት አገልጋይ ሆነ፣ ብዝሃነትን እና መደመርን አበረታታ፣ እና ከቨርጂኒያ ማደራጀት ጋር በመሆን የስደተኞች ቡድኖችን ፀረ-ኢሚግሬሽን ህግን ለመዋጋት አንድ ላይ ለማምጣት ሰርቷል። ረጅም ጊዜ የሚፈጅ የቅጣት ውሳኔን ለማስወገድ የወንጀል ፍትህ ማሻሻያ አበረታቷል፣ እና ከታሰረ በኋላ ስለማብቃት እና እንደገና ስለመቅረብ አስተምሯል። ፖሊስ ባልታጠቁ ጥቁሮች ላይ ለተሰነዘረው ጥይት ምላሽ፣ ማክሊን በ 2016 ውስጥ አናሳዎችን እና የዘር መድሎን የሚቋቋሙ አሜሪካውያንን መሠረተ። በ 2020 ክረምት ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ የሸንዶአህ ሸለቆ የህዝብ እኩልነት ኮሚሽን እንዲቋቋም ምክንያት ሆኗል፣ ይህም ለዜጎች ተቋማዊ ዘረኝነትን ለመዋጋት የጋራ መድረክን ይሰጣል።

ስለ Stan Maclin ተጨማሪ ለማወቅ

የMary Bowser ፎቶ

Mary Richards Bowser

ተለይተው የቀረቡ ሴት

Mary Bowser በRichmond ውስጥ የVan Lew ቤተሰብ ባሪያ ሆነው ተወለዱ። Elizabeth Van Lew በሰሜኑ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የከፈሉላቸው ሲሆን፣ የእርስ በእርስ ጦርነቱ ከመነሳቱም በፊት ነፃነታቸውን ሰጥተዋቸው ነበር። Bowzer የቤት ሠራተኛ በመምሰል ኮንፌደሬት አስተዳደር ሥር ወደነበረው ነጩ ቤተ መንግሥት ከተመለሱ በኋላ የVan Lewን ዩንየን ደጋፊ የስለላ ቡድን ሲረዱ ነበር።

ስለ Mary Richards Bowser ተጨማሪ ለማወቅ

ተጨማሪ ለጉልህ ሚናቸው ተለይተው የቀረቡ ሰዎችን ማየት ይፈልጋሉ?

በVirginia.gov ላይ የቀረበውን የVirginiaን ስመ ጥር ጥቁር ወንዶች እና ሴቶች የያዘ ዝርዝር መዝገብ ለመመልከት ከታች ያለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ሙሉ ዝርዝሩን ለመመልከት

ተማር

በVirginia ውስጥ ስለነበረው የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ተጨማሪ ለማወቅ ከታች ያሉትን ግብዓቶች ይመልከቱ።

መስህቦች

በVirginia ውስጥ ያለው የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ዙሪያ ተጨማሪ ለማወቅ በጣም ጥሩ ግብዓቶችን የሚያቀርብ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ መስህቦችን የያዘ አጭር ዝርዝር ከታች ማግኘት ይቻላል።

ተለይተው የቀረቡ መስህቦች

ተጨማሪ መስህቦች

ተጨማሪ የVirginia የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ መስህቦችን ለማየት ከታች ጠቅ ያድርጉ።

ተጨማሪ መሳህቦችን ለማየት

ክብረ በዓላት

በተለያዩ ዝግጅቶች ውስጥ በመሳተፍ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ መታሰቢያ ወርን በVirginia ያክብሩ።

በVirginia የሚካሄዱት የ2025 የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ መታሰቢያ ወር ዝግጅቶች