የVirginia የሠራተኛ ኃይል ግንኙነት በሥራ ፈላጊዎች እና አሠሪዎች መካከል ሁለገብ የማዛመድ አገልግሎት፣ የደሞዝ መረጃ፣ የክህሎት መስፈርቶች፣ የቀድሞ ወታደሮች አገልግሎቶች፣ የኢንዱስትሪ እና የሙያ መስክ አዝማሚያዎች እንዲሁም የስልጠና ዕድሎችን የሚመለከቱ መረጃዎችን ያቀርባል።
Virginia ውስጥ ጥሩ ሥራ ማግኘት ይፈልጋሉ? የVAWorks Mobile ስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ይፈልጉ። ወዲያውኑ ማንኛውንም የተለጠፈ ሥራ ይመልከቱ፣ በቁልፍ ቃላት እና ቦታ ይፈልጉ (ስቴት/ከተማ/ዚፕ ኮድ)፣ ውጤቶቹን በዝርዝር ቅርጸት ወይም ካርታ ላይ በመርፌ ተመላክቶ ይመልከቱ፣ በፈለጉት ኢንዱስትሪ ሥራዎቹን ያጣሩ። VAWorks Mobile ወደ ቀድሞ ፍለጋዎችዎ፣ በቅርብ የተመለከቷቸው ሥራዎች እና በእርስዎ ተወዳጅ ተደርገው የተለዩ ሥራዎች በቅጽበት ለመመለስ ያስችልዎታል።