የVirginia የሥራ ቅጥር ኮሚሽን (VEC) የስቴቱን የሥራ አጥነት ኢንሹራንስ (UI) የጥቅማ ጥቅሞች ፕሮግራም በማስተዳደር ያለ ጥፋታቸው ሥራቸውን ላጡ ግለሰቦች ጊዜያዊ የገንዘብ እርዳታ ያቀርባል። በVirginia የሥራ አጥነት ካሳ አዋጅ መሠረት በአሠሪዎች በሚከፈል ግብር የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ይህ ፕሮግራም ኢኮኖሚውን እያረጋጋ ሠራተኞችን፣ ቤተሰቦችን እና ማኅበረሰቦችን ይደግፋል። VEC በሌላ ስሙ "Virginia Works" ተብሎ በሚጠራው የVirginia የሠራተኛ ኃይል ልማት እና እድገት መምሪያ (DWDA) ስር ከሚተዳደሩ የሥራ ቅጥር አገልግሎቶች እና ስልጠናዎች ጋር ግለሰቦችን ያገናኛል።
የVirginia Works ጽሕፈት ቤቶች መሰረታዊ የሥራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች እርዳታ እና መልሶ ሥራ ማግኛ አገልግሎቶችን ማቅረብ ይችላሉ።