እውቂያ

  • ኢሜይልinfo@vbpd.virginia.gov
  • ስልክ(804) 786-0016
  • የፖስታ መላኪያ አድራሻ
    Virginia Board for People with Disabilities
    1100 Bank Street, 7th Floor
    Washington Building
    Richmond, VA 23219

ስለ ኤጀንሲው

የቨርጂኒያ አካል ጉዳተኞች ቦርድ ገዥውን፣ የጤና እና የሰው ሃብት ፀሀፊን፣ የፌደራል እና የክልል ህግ አውጪዎችን እና ሌሎች አካላትን በቨርጂኒያ አካል ጉዳተኞችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ይመክራል። የቦርዱ ዓላማ አካል ጉዳተኞች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው እንዲወስኑ፣ ራሳቸውን እንዲችሉ፣ ውጤታማ እንዲሆኑ እና በሁሉም የሕብረተሰብ ሕይወት ዘርፎች እንዲቀናጁ እና እንዲካተቱ የሚያስችል፣ የተቀናጀ ሸማችና ቤተሰብን ማዕከል ያደረገ፣ ሸማችና ቤተሰብ የሚመራ፣ ሁሉን አቀፍ የአገልግሎት ሥርዓት፣ የተናጠል ድጋፎችን እና ሌሎች የድጋፍ ሥራዎችን ለመሥራት የጥብቅና፣ የአቅም ግንባታ እና የሥርዓት ለውጥ ተግባራትን ማከናወን ነው።

ይህ የሚከናወነው በማዳረስ፣ በስልጠና፣ በቴክኒክ ድጋፍ፣ ማህበረሰቦችን በመደገፍ እና በማስተማር፣ እንቅፋት በማስወገድ፣ የስርአት ዲዛይን/ንድፍ፣ ጥምረት ልማት እና የዜጎች ተሳትፎ፣ ፖሊሲ አውጪዎችን በማሳወቅ፣ አዳዲስ አቀራረቦችን፣ አገልግሎቶችን በማሳየት እና ማህበረሰብን መሰረት ያደረገ አገልግሎት አሰጣጥን በማሳየት ነው። የቨርጂኒያ አካል ጉዳተኞች ቦርድ ነዋሪዎችን በቀጥታ አያገለግልም ነገር ግን የጥብቅና እና የአመራር ስልጠና ፕሮግራሞችን ይሰጣል።

ከክፍያ ነፃ 800-846-4464

ኦንላይን ያግኙን

የሚቀርቡ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች