ተገናኝ

ስለ ኤጀንሲው

የስቴት ኮርፖሬሽን ኮሚሽን (SCC) የማኅበረሰብ መገልገያ አቅራቢዎች፣ ኢንሹራንስ፣በስቴት የሚተዳደሩ የፋይናንስ ተቋማት፣ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች፣ የችርቻሮ ፍራንቻይዞች እና የባቡር መስመሮችን የመቆጣጠር ሥልጣን አለው። ለኮርፖሬሽኖች፣ የተገደቡ አጋርነቶች፣ ኃላፊነታቸው የተወሰነ ኩባንያዎች እና በመደበኛ የንግድ ልውውጥ ሕጎች ሥር ለሚጠየቁ እገዳዎች የስቴቱ ማዕከላዊ የመዝገብ ጽሕፈት ቤት በመሆን ያገለግላል። SCC አስተዳደራዊ፣ የሕግ አውጪ እና የሕግ ተርጓሚ ሥልጣኖች የሚመደቡለት ገለልተኛ የስቴት መንግሥት ቅርንጫፍ ነው። እንደ የመዝገብ ፍርድ ቤት የሚያገለግል ሲሆን፣ አስፈላጊ ኦኖ ሲገኝ መደበና ችሎቶችን ያካሂዳል። የSCC ውሳኔዎች ላይ ይግባኝ መጠየቅ የሚቻለው በVirginia ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብቻ ነው።

በVirginia ሕገ መንግስት 1902 ላይ የተመሰረተው SCC በማርች ወር 1903 ሥራ ጀምሯል። መጀመሪያ የተመሰረተው በVirginia የሚገኙትን የባቡር መስመር እና የቴሌፎን እና ቴሌግራፍ ኢንዱስትሪዎች ለመቆጣጠር ነበር። ከዚያን ጊዜ አንስቶ በVirginia ጠቅላላ ጉባዔ የቁጥጥር ሥልጣኑ ላይ ማስፋፊያዎች ተደርገውለታል።

ደንቦች እና መመሪያዎችን ከማውጣት ጀምሮ ትላልቅ በኢንቬስተር ባለቤትነት የተያዙ የማኅበርሰብ መገልገያ አቅራቢዎች የሚጠይቁትን የክፍያ ተመኖች እስከመመደብ ድረስ ሰፊ ሥልጣን ያለው SCC ሥልጣኑ የሚወሰነው በስቴት ሕገ መንግሥት እና በስቴት ሕጎች ብቻ ነው። ስድስት-ዓመት ለሚዘልቁ የስልጣን ዘመናት የሚያገለግሉት ሶስቱ የSCC ኮሚሽነሮች የሚመረጡት በጠቅላላ ጉባኤው ነው። ሙሉ ሰዓት የሚሰሩት ኮሚሽነሮች የSCCን ሥራ በመሪነት ይቆጣጠራሉ።

መገኛዎች እና ተጨማሪ እውቂያዎች

ዋና መገኛ

1300 East Main Street
Richmond, VA 23219
ለአቅጣጫዎች

የስልክ ቁጥሮች

ከክፍያ ነፃ 1-800-552-7945
አጠቃላይ (804) 371-9967
የፀሀፊ ቢሮ (804) 371-9733
የኢንሹራንስ ቢሮ (804) 371-9741

ኦንላይን ያግኙን

የሚቀርቡ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች