ተገናኝ

  • ስልክ(804) 786-6636
  • የፖስታ አድራሻ
    Judicial Inquiry and Review Commission
    P.O. Box 367
    Richmond, VA 23218

ስለ ኤጀንሲው

የፍትሕ አካላት ምርመራ እና ግምገማ ኮሚሽን የፍትሕ አካላትን የሥነ-ምግባር ጉድለት ወይም ከፍተኛ የአዕምሮ ወይም የአካል ጉዳተኝነት ውንጀላዎችን ለመመርመር በVirginia ሕገ መንግሥት ተመስርቷል። ኮሚሽኑ ሶድት ዳኛዎች፣ ሁለት ጠበቃዎች እና የሕግ ባለሙያ ያልሆኑ ሶስት ዜጎችን የያዙ ሰባት አባላት አሉት። አባላቱ አራት ዓመታት ለሚዘልቅ የሥልጣን ዘመን በVirginia ጠቅላላ ጉባኤ ይመረጣሉ።

ኮሚሽኑ በሁሉም የስቴት ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የስቴት ኮርፖሬሽን ኮሚሽን አባላት እና የVirginia የሠራተኛ ካሳ ኮሚሽን አባላት ላይ የሚሰነዘሩ የሥነ-ምግባር ጉድለት ቅሬታዎችን ለመመርመር ሠራተኞችን ይቀጥራል።

ኮሚሽኑ የፍትሕ አካላት የሥነ-ምግባር ጉድለት ወይም የአንድ ዳኛ ኃላፊነቶች ላይ ጫና ሊያሳድር የሚችል የአዕምሮ ወይም የአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ይመረምራል። የሥነ-ምግባር ጉድለት የሚከተሉትን የሚያካትት ሲሆን፣ በእነዚህ ብቻ ግን አይገደብም፦

  • ቤተሰብባዊ፣ ማኅበራዊ ወይም ሌሎች ግንኙነቶች በፍርድ ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ መፍቀድ
  • ተገቢውን የፍርድ ቤት ሥነ-ሥርዓት መጠበቅ አለመቻል
  • ትዕግስተኛ፣ ቁጥብ እና ጨዋ መሆን አለመቻል
  • የፍርድ ቤት ሥራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ አለመቻል
  • የፍትሕ እርምጃዎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ በሚችሉ የግል ውይይቶች ላይ መሳተፍ
  • በሂደት ላይ ያለ ጉዳይ ዙሪያ ለሕዝብ አስተያየት መስጠት
  • ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ከሚችልባቸው ሂደቶች ጋር በተያያዘ ራስን ማግለል አለመቻል
  • ከተከራካሪዎች ወይም ከጠበቃዎች ስጦታዎችን ወይም ሞገሶችን መቀበል
  • በሕግ ባለሙያ ሥራዎች ውስጥ መሳተፍ (ጡረተኛ ወይም ጊዜያዊ ዳኛ ካልሆኑ በስተቀር)
  • በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መሳተፍ
  • የአዕምሮ ወይም አካላዊ ጉዳት የአልኮል መጠጥ ወይም የአደንዛዥ እፅ ሱሰኝነት፣ ከፍተኛ እርጅና ወይም ከባድ የአካል ወይም የአዕምሮ በሽታን ሊያካትት ይችላል።