የቀድሞ ወታደሮች አገልግሎቶች መምሪያ (DVS) በሚከተሉት ስድስት የአገልግሎት አቅርቦት ክፍሎች የተደራጀ ነው፦ ጥቅማጥ ቅሞች፣ የቀድሞ ወታደሮች ትምህርት፣ የእንክብካቤ ማዕከላት፣ የቀድሞ ወታደሮች የመቃብር ቦታዎች፣ የVirginia War Memorial እና የVirginia የቀድሞ ወታደሮች እና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ ፕሮግራም። የሚከተሉት በዜጎች የተዋቀሩ ሶስት ቦርዶች ከኤጀንሲው ጋር በቅርበት በመሥራት አገልግሎቶች ለVirginia የቀድሞ ወታደሮች በፍጥነት እንዲደርሱ ድጋፍ ያቀርባሉ፦ የቀድሞ ወታደሮች አገልግሎቶች ቦርድ፣ የቀድሞ ወታደሮች አገልግሎት ድርጅቶች የተቀናጀ የቀድሞ ወታደር አገልግሎት ድርጅቶች አመራር ምክር ቤት እና የቀድሞ ወታደሮች አገልግሎት ፋውንዴሽን።