የግምጃ ቤት መምሪያ እንደ ማዕከላዊ የስቴት ኤጀንሲ በማገልገል ለኮመንዌልዙ ኤጀንሲዎች እና ተቋማት ስቴት አቀፍ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ያቀርባል። ግምጃ ቤቱ በሚከተሉት ስድስት የአገልግሎት መስኮች ይከፋፈላል፦ አጠቃላይ አስተዳደር፣ የብድር አስተዳደር፣ የስጋት አስተዳደር፣ የሥራ እንቅስቃሴዎች፣ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር እና ኢንቬስትመንቶች እና ባለቤት ያልተገኘላቸው ንብረቶች። የስቴት ግምጃ ቤት ኃላፊው በቀጥታ ለፋይናንስ ሴክሬተሪው ተጠሪ የሚሆኑ ሲሆን፣ የዚህ የካቢኔ ሥልጣን ሹም ደግሞ በቀጥታ ለገዥው ተጠሪ ይሆናሉ። ግምጃ ቤቱ የስቴት ገንዘቦችን ኢንቬስትመንት የመቆጣጠር፣ የኮመንዌልዙን የአጭር እና የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ፍላጎቶች የማሟላት እና የማስተዳደር፣ የስቴቱን ባለቤት ያልተገኘላቸው ንብረቶች እና የመንግሥት ወረሳ ሕጎች የማስተዳደር፣ የኢንሹራንስ እና የስጋት አስተዳደር ፕሮግራሞችን የማስተዳደር፣ የስቴቱን የባንክ አገልግሎት አውታር የማስተዳደር፣ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ፕሮግራሞችን የማዳበር እና የአገልግሎቶችን አሰጣጥ የመፈተሽ ኃላፊነቶች ይኖሩታል።