የአነስተኛ ንግድ ሥራዎች እና አቅራቢዎች ብዝሃነት መምሪያ (SBSD) የአነስተኛ እና በሴቶች እና የአናሳ ማኅበረሰብ አባላት ባለቤትነት የተያዙ ንግድ ሥራዎቻችን በVirginia የግዢ ዕድሎች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚሠራ የስቴት ኤጀንሲ ነው። SBSD የሚከተሉትን ሁለት የእውቅና ፕሮግራሞች የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት፦ በVirginia የSWaM የግዢ ተነሳሽነት ሥር የሚመደቡ አነስተኛ እና በሴቶች እና በአናሳ ማኅበረሰብ አባላት ባለቤትነት የተያዙ የንግድ ሥራዎች እንዲሁም የአሜሪካ የፌደራል ትራንስፖርት አገልግሎት መምሪያ የተገለሉ የንግድ ሥራዎች ድርጅት ("DBE") ፕሮግራም። በተጨማሪም SBSD ከሌሎች ኤጀንሲዎች እና መምሪያዎች ጋር በመተባበር በሚያቀርባቸው የንግድ ሥራ ልማት እና የግዢ ጥብቅና ፕሮግራሞች አማካኝነት እውቅና ላገኙት የንግድ ሥራዎቻችን ድጋፍ ያቀርባል።