ተገናኝ

  • ስልክ(804) 497-7100
  • የፖስታ አድራሻ
    Department of Motor Vehicles
    P.O. Box 27412
    Richmond, VA 23269

ስለ ኤጀንሲው

የሞተር ተሽከርካሪዎች መምሪያ (DMV) በርካታ የደንበኛ አገልግሎት ማዕከሎች፣ የDMV Select አጋር ጽሕፈት ቤቶች፣ የDMV Connect ተንቀሳቃሽ ጽሕፈት ቤቶች፣ የኤጀንሲው ድር ጣቢያ እና የማኅበራዊ ሚዲያ መለያዎች፣ የክብደት መለኪያ ጣቢያዎች እና የስልክ ጥሪ ማዕከሎችን በሚያጠቃልል መረብ አማካኝነት አገልግሎት ያቀርባል። የDMV ተሞክሮዎን ወደ dmvNOW.com በመግባት ይጀምሩ፤ እዚህም ከ 50 በላይ የDMV ግብይቶችን ማከናወን እና ለREAL ID እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። የDMV በጣም የሚታዩ እና በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉት ምርቶች የአሽከርካሪ፣ የተሽከርካሪ እና የጭነት ወይም የሰው አመላላሽ ማረጋገጫዎችን ያካትታሉ። DMV ስቴት አቀፍ የአገልግሎት አሻራውን ጥቅም ላይ በማዋል ከሌሎች ኤጀንሲዎች ጋር በሚደረጉ አጋርነቶች ተጨማሪ ምርቶች እና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ይሠራል። የVirginia ነዋሪዎች የወሳኝ ኩነት መዝገቦችን (የትውልድ፣ የሞት፣ የጋብቻ እና የፍቺ የምስክር ወረቀቶች) እና የአደን እና ዓሳ ማጥመጃ ፈቃዶችን በሁሉም የDMV የደንበኛ አገልግሎት ማዕከሎች በኩል ማግኘት ይችላሉ። የE-ZPass የመንገድ ክፍያ ትራንስፖንደሮች በበርካታ ቦታዎች ይገኛሉ።

መገኛዎች እና ተጨማሪ እውቂያዎች

ብዙ መገኛዎች አሉ

መገኛዎችን ለመፈለግ

ኦንላይን ያግኙን

የሚቀርቡ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች