DHRM የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉት፦
DHRM ከሰዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎች እና ሂደቶችን ለማስተዳደር የቴክኖሎጂ እና የሥርዓት መፍትሄዎችን የማስተዋወቅ ኃላፊነት አለበት። በሥራ ቦታ ላይ ብዝሃነት፣ ፍትሐዊነት እና አካታችነትን ማስፈን ላይ ሰፋ ያለ ትኩረት በማድረግ እኩል የሥራ ዕድልን ተደራሽ ማድረግ በከፍተኛ ደረጃ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል። ባልተማከለ የሰው ኃይል አካባቢ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው DHRM የኮመንዌልዝ ኤጀንሲዎች ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞች የሚያደርጓቸው የሥራ እንቅስቃሴዎችን አፈጻጸም ውጤታማነት የሚገምገም ፕሮግራም የማከናወን ግዴታ አለበት።