የአካባቢ ጥራት መምሪያ (DEQ) የአየር ጥራት፣ የውሃ ጥራት፣ የውሃ አቅርቦት እና የመሬት ጥበቃ ዙሪያ የተደነገጉትን የስቴት እና ፌደራል ሕጎች እና ደንቦች ያስተዳድራል። ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች ፕሮግራሞች አካባቢን ለመጠበቅ እና ብክለትን ለመከላከል የንግድ ሥራዎች እና የአካባቢ መስተዳድሮች ያላቸውን አቅም ማሳደግን የመሳሰሉ ሌሎች የተለያዩ የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴዎችን ያከናውናሉ። ኤጀንሲው ለአየር እና የውኃ ጥራት ማሻሻያዎች፣ የባህር ዳርቻ ዞን አስተዳደር እና የተበከለከለ መሬት እና ውኃ የማጽዳት ሥራዎች ላይ ቴክኒካዊ እና ገንዘብ-ነክ ድጋፍ ይሰጣል። DEQ በስድስት ክልላዊ ጽሕፈት ቤቶቹ አማካኝነት ጊዜያዊ ፈቃዶችን ይሰጣል፣ የጥራት ምርመራዎች እና ክትትሎችን ያከናውናል እንዲሁም ደንቦች እና ጊዜያዊ ፈቃዶችን ያስከብራል።
1105 East Main Street, Ste. 1400
ሪችመንድ፣ VA 23219