ተገናኝ

  • ኢሜይልpio@vdem.virginia.gov
  • ስልክ(804) 267-7600
  • የፖስታ አድራሻ
    Department of Emergency Management
    9711 Farrar Court
    Suite 200
    North Chesterfield, VA 23236

ስለ ኤጀንሲው

የVirginia የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር መምሪያ (VDEM) የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ዙሪያ በሚተገብራቸው አራት ምዕራፎች አማካኝነት ግብዓቶች እና ባለሙያዎችን ለማቅረብ ከአካባቢ መስተዳድሮች፣ የስቴት እና የፌደራል ኤጀንሲዎች እና በጎ ፈቃደኛ ድርጅቶች ጋር በትብብር ይሠራል። VDEM የስቴቱን የድንገተኛ አደጋ ዕቅዶች የሚያወጣ እና የሚያስተዳድር ሲሆን፣ አካባቢ ተኮር የድንገተኛ አደጋ አሠራሮችን በመንደፍ ረገድ ማኅበረሰቦችን ይረዳል።

ኤጀንሲው ከዚህ በተጨማሪም ከአካባቢያዊ አስተዳደሮች ጋር አብሮ በመሥራት ማኅበረሰቦቻቸው ተጋላጭ ለሆኑባቸው ልዩ አደጋዎች የተቀረጹ ውጤታማ እና ዘላቂ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ዕቅዶችን ለማውጣት ይረዳል። VDEM ለአደጋዎች እና ተከትሎ ለሚፈጠረው ነገር የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎችን ለማዘጋጀት በድንገተኛ አደጋ አስተዳደር፣ የአደገኛ ቁሳቁሶች ምላሽ እና የፍለጋ እና ማዳን ሥራዎች ዙሪያ የስልጠና ኮርሶችን ይሰጣል። በመላው ስቴት የሚካሄዱት ልምምዶች እና መለማመጃ እንቅስቃሴዎች ቁጥጥር በሚደረግበት ሁኔታ ውስጥ እነዚህን ክህሎቶች ተግባር ላይ ማዋል የሚቻልበት ዕድል ይሰጣሉ። የአካባቢ መስተዳድሮች ለቀውሶች ምላሽ ለመስጠት እርዳታ ሲያስፈልጋቸው የሚደውሉት ለVDEM ነው።

ስቴቱ የምላሽ አሰጣጥ ሥራዎችን ለማስተባበር እና በነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ለገዥው የሁኔታ ሪፖርቶችን ለማቅረብ በVirginia የድንገተኛ አደጋ ሥራዎች ማዕከል ውስጥ የሚገኙትን ሠራተኞች ብዛት ይጨምራል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ገዥው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃሉ። በፌዴራል ደረጃ የታወጀ የአደጋ ጊዜን ተከትሎ ለተጠቁ ግለሰቦች እና የመንግሥት ኤጀንሲዎች የእርዳታ ፕሮግራሞችን ለማስተባበር እና ለማቅረብ VDEM ከFEMA ጋር በትብብር ይሠራል።

መገኛዎች እና ተጨማሪ እውቂያዎች

ብዙ መገኛዎች አሉ

መገኛዎችን ለመፈለግ

ኦንላይን ያግኙን

የሚቀርቡ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች