የVirginia የእርጅና እና የማገገሚያ አገልግሎቶች መምሪያ ከማኅበረሰብ አጋሮች ጋር በመተባበር በእድሜያቸው ለገፉ የVirginia ነዋሪዎች፣ አካል ጉዳተኛ ለሆኑ የVirginia ነዋሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው የሥራ ዕድል፣ የኑሮ ጥራት፣ ደኅንነት እና ራስን የመቻል አቅምን ለማሻሻል የሚረዱ ግብዓቶች እና አገልግሎቶችን ያቀርባል እንዲሁም ለእነዚህ ግብዓቶች እና አገልግሎቶች ይሟገታል። DARS የአዋቂዎች ጥበቃ አገልግሎቶች ክፍልን፣ የማኅበረሰብ ተኮር አገልግሎቶች ክፍልን፣ የአካል ጉዳተኝነት ግምገማ አገልግሎቶች ክፍልን፣ የማገገሚያ አገልግሎቶች ክፍልን፣ የእርጅና ጉዳዮች ክፍልን፣ Wilson የሠራተኛ ኃይል እና የማገገሚያ ማዕከልን፣ የማኅበረሰብ ትስስር ጽሕፈት ቤትን እና የስቴት የረጅም ጊዜ እንክብካቤ እንባ ጠባቂ ጽሕፈት ቤትን ያካትታል።